About Qene Academy ስለ ቅኔ አካዳሚ

‘ሁሉንም ባለድርሻ አካላት በማሳተፍ የትምህርትን ጥራት በማስጠበቅ በእውቀትና ሥነ-ምግባር የታነፀ፣ሀገሩን የሚወድ ትውልድ ለማፍራት ጠንክረን እንሰራለን!!’

ርእይ Vision

በእውቀትና በሥነ ምግባር የታነፀ፣ ታሪኩንና ባህሉን የሚያከብርና የሚጠብቅ ትውልድ በመፍጠር በሀገር አቀፍ ደረጃ በትምህርትና ሥልጠና ጥራት በ2030 ዓ.ም የመሪነት ሚናውን ሲወጣ ማየት

ተልእኮ Mission

  • ብቃት ያላቸው ባለሙዎችን በማቀፍና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመታገዝ ጥራት ያለውና ተወዳዳሪ የሆነ ትምህርትና ሥልጠና መስጠት
  • የኢትዮጵያን ታሪክና ባህል በጥልቀት መርም ለማወቅ የሚያስችለውን ትምህርት ለዳጊው ትውልድ በማስተማር ሀገሩን እንዲወድ ማድረግ
  • ወላጆችንና ባለ ድርሻ አካላትን በባለቤትነት በማሳተፍ አገራዊና ማኅበራዊ ግዴታውን መወጣት
  • ለመምህራንና ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች የአቅም ማጎልበቻ ሥልጠና በመስጠት ትጉህና ተነሳሽነት ያላቸው ባለሙያዎችን መፍጠር
  • በኢትዮጵያ በሁሉም ክልሎች ቅርንጫፍ ት/ቤቶችን በመክፈት አስተማማኝ ዕድገት ማስመዝገብ
  • ሁለገብ የሆነ የሥልጠና ማዕከል ማቋቋም

እሴቶች Core Values

  • በሥነ ምግባር የታነፀ ትውልድ መፍጠር
  • መልካም አስተዳደርን ማስፈን
  • የትምህርትና ሥልጠና ጥራትን ማረጋገጥ
  • አገራዊና ማኅበራዊ ግዴታን መወጣት
  • አዳዲስ የአሠራር ሥልቶችን መቀየስ
  • ደህንነቱ የተጠበቀ የመማር ማስተማር ባህል ማስፈን
  • ተመጣጣኝ ትርፍ ማስገኘት
  • ተደራሽ የሆኑ የጥናትና ምርምር ሥራዎች ማስፋፋት

የወላጆችንና የሠራተኞችን ፍላጎት ማዕከል ያደረገ ትግበራ ማከናወን